Fana: At a Speed of Life!

የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ በጅቡቲ ቆመው የነበሩ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎች ቁልፎች ተመላሽ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ አዲስ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የኩባንያው ንብረት የሆኑ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ቁልፎች ተረከቡ።
ከታገዱት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ ለስራ ወደ ጂቡቲ የተጓዙ እና ወደ ሀገር ቤት ሳይመለሱ የቀሩ 179 የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና አራት የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ /ቦቴ/ ከጅቡቲ ለመመለስ ውይይት ሲካሄድ ቆይቷል።
በዚህም በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር ከባድ ተሽከርካሪዎችን ለመመለስ ባከናወነው ስራ ሊመለሱ እንደቻሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ህወሓት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ከመፈፀሙ ጥቂት ቀናት በፊት የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያ አስተዳደር ሃላፊዎች ከጅቡቲ ወደብ እቃዎችን ለማምጣት በሚል 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጅቡቲ ወስዶ እንዳቆማቸው ነው የተገለፀው።
ትራንስ ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በገንዘብ በማገዝ ፣ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና በሌሎች ወንጀሎች በመጠርጠሩ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሸከርካሪዎቹ እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላልፎ እንደነበረ ተጠቁሟል።
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት እና ከሚመለከታቸው የጅቡቲ መንግስት አካላት ጋር በመተባበር ፤ የጅቡቲ መንግስት ከአሽከርካሪዎቹ የተሽከርካሪዎቹን ቁልፍ መረከቡ ነው የተነገረው።
ከእነዚህ አሽከርካሪዎች መካከል ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆኑት 14ቱ በስተቀር ቀሪዎቹ በጅቡቲ የስደተኞች መጠለያ ይገኛሉ ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.