የበረሃ አንበጣ መንጋ በሶማሌ ክልል ጉዳት እያደረሰ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የበረሃ አንበጣ መንጋ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አስታወቀ።
ቢሮው የበረሀ አንበጣ መንጋው በክልሉ በሚገኙ 10 ዞኖች በአርሶ አደሩ ሰብልና በአርብቶ አደሩ የእንስሳት ግጦሽ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም አስታውቋል።
የሶማሌ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱላሂ አደም ዩሱፍ አንበጣው በድንበር አካባቢ በሚገኙ ዞኖች በስፋት እየተሠራጨ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይም ከአጎራባች ሃገራት ጋር በመተባበር የበረሃ አንበጣ ሥርጭቱን ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ከሲቲ ዞን በስተቀር በሁሉም የሶማሌ ክልል ዞኖች የበረሃ አንበጣ ሥርጭቱ እየተስፋፋ በሰብልና ግጦሽ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ቢሮው የአንበጣውን ስርጭት ለመቆጣጠርም ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!