Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የ2013 ክልል አቀፍ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የ2013 ክልል አቀፍ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄደ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ዘርፍ አስተባባሪና የደቡብ ክልል እርሻና ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በክልሉ በ2012 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት 355 ሺህ 654 ሄክታር መሬት የለም ሲሆን በዚህ አመትም ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የተሻለ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ተግባራትን ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

የ2013 ክልላዊ ንቅናቄ “የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ለሁለተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንደሚካሄድም ተናግረዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ከተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና ልማት ጎን ለማንም የመስኖ ልማትን በማጠናከር ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ ዘመናዊ ግብርናን እውን ለማድረግ በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ መሆኑን አቶ አንተነህ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

ከጥር 18 ጀምሮ የሚካሄደው ንቅናቄ ቆይታውም ለ30 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዚህም 357 ሄክታር መሬት ይለማል ተብሎ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.