Fana: At a Speed of Life!

ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ብቻ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደማያስችሉና የባለድርሻ አካላትን ርብርብ እንደሚጠይቁ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

ዶክተር ሊያ ይህን የገለፁት የጤና ሚኒስቴር በቀጣዮቹ ዓመታት ለትግበራ ያዘጋጀውን የጤናው ዘርፍ የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ እና የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለህዝብ ተውካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለተጠሪ ተቋማት ተወካዮች በቢሾፍቱ ከተማ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

መሪ ዕቅዱ 14 የትኩረት አቅጣጫዎች፣ አምስት የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች እና አምስት ግቦች እንዲሁም 76 ጠቋሚዎች እንዳሉት ገልፀው ቁልፍ ጉዳዮች ያሏቸውን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል።

ከህብረተሰቡ ፍላጎት ማደግና መጨመር፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መስፋፋት እንዲሁም ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ ተደራሽ የጤና አገልግሎቶችን ከማቅረብ አኳያ ዛሬም ተግዳሮቶች መኖራቸውን ዶክተር ሊያ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የጤና ትምህርት ጥራት፣ የጤና መሰረተ ልማት ፍትሃዊ ተደራሽነት ለሰይ ይበልጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ሚኒስትሯ፥ በሱስ የሚያዙ ሰዎች መበራከት፣ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር እና በስርዓተ ፆታ ላይ የሚታዩ ችግሮች ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

የጤናው ዘርፍ በቂ በጀት እንዳለው ተደርጎ የሚነገር የተሳሳተ አስተሳሰብ መኖሩን በመጥቀስም በቀጣይ ጥራት ያላቸውን የጤና አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ስለሚጠይቅ የተከበረው ምክር ቤት አባላት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከ21 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ለስራው እንደሚያስፈልግና ወጪውም በመንግሥትና በአጋር አካላት ድጋፍ እንደሚሸፈንም አውስተዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አመራሮች እንዲሁም የተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጤና ሚኒስቴር ዳይሬክተሮችና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.