የሶማሌ ክልል መንግስት እና የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግስት እና የክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ይገኛል።
ግምገማው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ አቶ ኢብራሒም ዑስማን እና የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሐመድ ሻሌ በተገኙበት ነው እየተካሄደ ያለው።
በዋናነት ግምገማው አስፈፃሚው አካልና ፅህፈት ቤቱ በመሰረታዊ የመንግስት አሰራሮች ላይ ያሉ ሂደቶች እንዲሁም በተያዘው አመት የተጀመሩም ይሁን ካለፈው አመት ወደዚህ የተሻገሩ ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን ጠንካራና ደካማና ጎኖች በመፈተሽ በቀጣይ የተሻለ ስራና አገልግሎት መስጠት ማስቻል መሆኑ የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የስራ አፈፃፀም ግምገማው ለአምስት ቀናት እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!