ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጋምቤላ ከተማ ያስገነቡትን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቁ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ካስገነባቸው 20 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 11ኛውን በጋምቤላ ክልል አስመረቀ፡፡
ጽህፈት ቤቱ በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ቀበሌ 05 በ13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ያስገነባውን ብርሃን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመርቋል፡፡
በምረቃውቃት ስነ-ስርዓት ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያችው፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል::
ትምህርት ቤቱ በውስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራ፣ የቤተ መጽሐፍት፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ነው፡፡
ትምህርት ቤቱ በሁለት ፈረቃ 1 ሺህ 800 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡
ጽህፈት ቤቱ በዛሬው እለት ያስመረቃቸውን ጨምሮ እንደ ሃገር ግንባታችው ተጠናቆ ያስመረቃቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር 11 የደረሱ ሲሆን ቀሪዎቹን በቅርብ ቀን እንደሚያስመርቅም አስታውቋል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!