የኤርትራ ስደተኞች በሚገኙባቸው ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ መጠለያ ካምፖች ጉብኝት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራ ስደተኞች በሚገኙባቸው ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ መጠለያ ካምፖች ጉብኝት ተካሄደ።
በጉብኝቱ ላይ የስደተኞችና እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ
ተወካይ አን አሌን ኤንኮንትር የተመራ ልዑክ ተሳትፏል።
የጉብኝቱ ዓላማም በስደተኞች ጣቢያ በትግራይ ክልል ከነበረው ህግን የማስከበር እርምጃ በኋላ የጀመረውንን መሰረታዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦት ለመደገፍ እና ለመመልከት ነው ተብሏል።
በተያዘው የፈረንጆቹ የጥር ወር በጣቢያዎቹ ያለው የምግብ ስርጭት እና የተለያዩ አገልግሎቶች አቅርቦትም የጉብኝቱ አንድ አካል ነበሩ።
በዚህ ወቅትም ከአዲ ሃሩሽ የስደተኞች ጣቢያ የስደተኞች ማዕከላዊ ኮሚቴ ጋር ከደህንነት እና ከአገልግሎት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ውይይት መካሄዴ ተጠቁሟል።
የስደኞቹ ተወካዮችም በጣቢያ ስላሉ ሁኔታዎች እና የአገልግሎት ጥራት የሚሻሻልበትን በተመከተ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
የስደተኞችና እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ተወካይ አመራሮች የስደተኞችን ደህንነት እና ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!