Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የስራ ኃላፊዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ እና የአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ህብረት የስራ ኃላፊዎች ጋር መከሩ፡፡

በውይይቱም አምባሳደሯ በትግራይ ክልል ስለተካሄደው የህግ ማስከበር፣ በክልሉ ስላለው ተጨባጭ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ መሰረተልማቶችን ጠግኖ ወደ ስራ ማስገባት እና ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናሮ መቀጠሉንም አስረድተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቶማስ ቶቤ ኢትዮጵያ በቀጠናው ወሳኝ መሆኗን በመግለፅ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ተናግረዋል፡፡

በፓርላማው የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዊቶልድ ጃን ዋዥኮውስኪ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መረጋጋት አስፈላጊነትን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በውይይቱ ከአውሮፓ የውጭ አገልግሎት ጎዳይ፣ አለማቀፍ የትብብር ኮሚሽን እና ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የተውጣጡ አባላትም ተሳትፈዋል፡፡

አምባሳደር ሂሩት ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍና ሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲሁም ስለ ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.