የሰሜንና ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የምክክር መድረክ በባህር ዳር ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜንና ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የምክክር መድረክ ነገ በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል ።
የሰሜንና ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ የምክክር እና የትብብር ፎረም ነገ ”መልካም ጉርብትና ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡
የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ጠንካራ የህዝብ ለሕዝብና የመንግስታት ግንኙነቶችን በመፍጠር ፣ በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር እና ችግሮችን በሰላማዊና በሰለጠነ ዴሞክራሲያዊ መንገድ እና በዘለቄታዊነት መፍታት ያስፈልጋል ብሏል ፌዴሬሽኑ፡፡
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት እንዲኖር ፣ ጠንካራ የመንግስታ ግንኙነት እንዲፈጠር ፣ ያሚነሱ አለመግባባቶችና ግጭቶች የመከላከያና የማስወገጃ ስልቶችን በማጥናት የአሰራር ስርዓትና ስልት የመዘርጋት እንዲሁም ስልቱን ተቋማዊ አደረጃጀት እንዲኖረው የማድረግ ስልጣንና ኃላፊነት ያለው መሆኑን አስታውሷል፡፡
በዚህው መሠረት የሰሜንና ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የምክክር መድረክ በባህርዳር ከተማ የሚካሄድ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ የትብብር ፎረም መመሥረት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ”በሕብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት የክልሎች የርስበርስ ግንኙነት ሥርዓት አስፈላጊነት” በሚል የተዘጋጀ ጥናታዊ ፁሑፍ በዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!