የዓለም አቀፉ የንፁሃን የጅምላ ዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የንፁሃን የጅምላ ዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።
ይህ ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ መከበር የጀመረወ ከዛሬ 76 ዓመት በፊት በአዶልፍ ሒትለር መራሹ የጀርመን የበላይነት አቀንቃኝ ናዚ ቡድን በአይሁዳውያን ላይ የተፈፀመውን ጅምላ ጭፍጨፋ መሰረት በማድረግ ነው።
ከፈረንጆቹ ከ2005 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል።
በአዲስ አበባ የእስራኤልና የጀርመን አምባሳደሮችን ጨምሮ የየመንግሥታቱ ድርጅት ተወካዮች ባሉበት በኢሲኤ እየተከበረ ነው።
ከዛሬ 76 ዓመት በፊት 6 ሚሊየን አይሁዳውያን በአውሮፓ ምድር በጅምላ የተጨፈጨፉበትና ሌሎች ሚሊዮኖች የተገደሉበት ጊዜ ነበር።
በመድረኩ የጀርመኑ አምባሳደር ስቴፈን “ጀርመን በናዚ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ ዕውቅና ትሰጠዋለች፣ በታሪክም ወንጀሉን ለልጅ ልጆቻችን ዳግም እንዳይደገም እንዘክራለን” ብለዋል።

የፀረ ፅዮናዊያን እንቅስቃሴንም አጥብቃ እንደምታወግዝና እንደምትታገል አረጋግጠዋል።
የናዚ ድርጊት ጥላቻ፣ ዘር ማጥፋት፣ አክራሪ ብሔርተኝነትን በግለሰብ ደረጃም ሆነ ቡድን ማስወገድና አብሮነትና መቻቻልን ማጎልበት እንደሚገባ ከታሪክ መማር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገሮች ለትናንት ዕውቅና ሰጥተው የወደፊት በጋራ ግንኙታቸውን እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል።
የእስራኤሉ አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ በበኩላቸው “ከ6 ሚሊየኖች ንፁሃን አይሁዳውያን ጭፍጨፋ አስከፊነት በማስታወስ ዛሬ የዘር ተኮር ጥላቻና ዘር ማጥፋትን ለማስወገድ በጋራ መስራት ይገባል” ብለዋል።
“ዕለቱን ከጀርመን ጋር ስንዘክር አንድም የይቅርታን ኃይል፣ አንድም ከታሪክ በመማር ለሰው ልጅ ዕኩል ክብር መስጠት እንደሚገባ ለማሳየት ነው” ሲሉ መናገራቸውን
“ቀኑን በዚህ አግባብ ለቀጣይ ትውልድ እንዘክራለን” ነው ያሉት።
በመድረኩ ከጥቃት የተረፉ ሰዎች በስካይፒ ትውስታቸውን አጋርተዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!