500 ትምህርት ቤቶችን ያቀፈ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮጀክት ይፉ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከህፃናት አድን ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን 500 ትምህርት ቤቶችን ያቀፈ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮጀክት ይፉ አደረገ።
በዚህ ሀገር በቀል የትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮጀክት ከ163ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባው አካል እንደሚሆኑ ተነግሯል።
ፕሮግራሙ በ5 ክልሎች ውስጥ ባሉ 13 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው የተገለፀው።
በፕርግራሙም ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚካተቱ ሲሆን ለአንድ ዓመት እንደሚቆይም ተነግሯል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዬን ማቲዎስ ፕሮጀክቱ የነገ ተስፋ የሆኑ ህፃናት ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ እና በትምህርት ቤት ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ ትልቅ አስተዋጸዖ አለው ብለዋል።
የህፃናት አድን ድርጅት በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ኢኪን ኦጉቶጉላሪ በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት ድርጅቱ ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው መስኮች መካከል አንዱ በመሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የምገባ ፕሮግራሙ በተፈጥሮ እና በአንዳንድ ምክንያቶች የተጎዱ እና ከዚህ በፊት ድጋፍ ያልተደረገላቸው አካባቢዎችን የሚያካትት መሆኑም ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ይፋ የሆነው ዓለምአቀፍ ትብብር ለትምህርት በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ አማካኝነት መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ቀደም ሀገር በቀል የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!