የህወሓት ጁንታ መመታት የኢትዮጵያን አንድነት ለሚጠሉ ሀይሎች አንገት የሚያስደፋ ተግባር ነው- አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ጁንታ መመታት የኢትዮጵያን አንድነት ለሚጠሉ ሀይሎች አንገት የሚያስደፋ ተግባር መሆኑን የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ተናገሩ።
የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ባለፉት ጊዜያት በህዝቦች መገዳደል ትርፍ ለማግኘት የሚሰሩ ሀይሎች ነበሩ ብለዋል።
የህውሓት ጁንታ ደግሞ የጥፋት ሀይሎች የበላይ ቁንጮ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ሀገር እንድትበታተን ሲሰራ የነበረው የህወሓት ጁንታ መወገዱ ተመሳሳይ ህልም ያላቸውን ቡድኖች አንገት አስደፍቷል ያሉት አቶ ሙስጠፌ፤ ለዘላቂ ሀገራዊ አንድነት ይህ እኩይ አስተሳሰብ እንዳያንሰራራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል በሱማሌ ክልል የሰፈነው ሰላምና መረጋጋት የክልሉ ህዝብ ለሰላም የሚሰጠው ዋጋ ትልቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በሱማሌ ክልል ዜጎች በሀይማኖታቸውም ሆነ በብሄራቸው ሳይሸማቀቁ በነጻነት የእለት ተለት እንቅስቃሴያቸውን ከመተግበርም በላይ በነጻነት ሀሳባቸውን መግለጽ እንዲችሉ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
ብስራት መለሰ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!