ጠ/ሚ ዐቢይ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጉብኝት ያካሄዱት ረፋድ ላይ ነው፡፡
ድርጅቱ ለተጎዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ለሲቪሎች ሰው ሠራሽ አካል ይሰራል፡፡
በሕግ ማስከበር ሂደቱና በሌሎችም ጊዜያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው በበጎ ፈቃደኞችና በድርጅቱ ባለሞያዎች የሚከናወነውን የሰው ሠራሽ አካል ማምረቻ ድርጅት ሠራተኞች የሚደነቅ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይህንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ሰሎሞን አማረን የመሰሉ ወገኖች ሊበረታቱ ይገባልም ብለዋል።
በአላዛር ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!