ተጨማሪ 549 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 266 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 3 የላቦራቶሪ ምርመራ 549 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 266 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 2 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት 2 ሺህ 85 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 647 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 230 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 942 ሺህ 333 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!