Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ተመሥገን ጥሩነህ የሽኝት ዝግጅት የተገኙ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች መልዕክት አስተላልፈዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የአቶ ተመሥገን ጥሩነህ የሽኝት ዝግጅት ላይ የተገኙ የክልል ርእሳነ መሥተዳድሮች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሰው በጠፋበት ሰው ሆነው የተገኙ፣ ብልህ፣ አስተዋይና አርቆ አሳቢ የሆኑ ናቸውም ብለዋል።

ሀገራችን ብዙ ፈተናዎችን አልፋለች፣ አሁንም ሊኖር ይችላል የሚቀር ቀርቶ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ነው ያሉት።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ እና የአማራ ክልል ሕዝቦች ከመዋሰን በላይ በደም የተሳሰረ፣ ይለይ ቢባል የማይለይ ሕዝብ ነው ብለዋል።

የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ሆኖ ሳለ በጥቂት ቡድኖች ችግር ላይ ወድቋል፤ ይሄን ችግር ለመፍታት እስካሁን ያለውን ወንድማማችነት እና የሁላችንንም ርብርብ ያስፈልገናል ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙሰጠፌ መሐመድ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ችግር በነበረበት ጊዜ አቶ ተመሥገን ድጋፍ ያደረጉልን መሪ ናቸው ብለዋል።

የሶማሌ ክልል መዋቅር ፈርሶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሙስጠፌ ክልሉ መዋቅሩ እንዲስተካከል ከፍተኛ ሥራ መሥራታቸውንም ተናግረዋል።

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ጁንታው የደገሰውን እልቂት ጉም ሆኖ እንዲቀር፣ የለኩሱት እሳት ራሳቸውን እንዲያቃጥልና ለእኛ ብርሃን እንዲወጣ ላደረጉ፣ የትግራይ ሕዝብ ከአፈና እንዲወጣ፣ የተደበቀውን ሕብረ ብሔራዊነት እንዲታይ ላደረጉ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጅሉ ከነበረው ችግር አንፃር አቶ ተመስገን ክልሉን በሁለት እግሩ ያቆሙታል ወይ የሚል ጥያቄ ነበረኝ አሁን ግን ጥያቄዬ ተመልሶ ክልሉ ወደ ትክክለኛ አቋሙ መጥቷል ነው ያሉት።

የጋምቤላ ክልልና ሕዝብ ከአማራ ክልል ጋር በጋራ ይሠራል ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል።

የአፋር ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ኡሌማ አቡበክር የአፋርና የአማራ ክልል ሕዝቦች ጉርብትና እንዲጠናከር ሠርተዋልም ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.