ለጥር 23 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሄድ እውቅና የተሰጠው አካል የለም – የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሄድ እውቅና የተሰጠው አካል ያለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
ኮሚሽኑ በዕለቱ እውቅና የተሰጠው ሰልፍ እንዳለ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑንም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት አስተዳደር ጉዳዩች ዘርፍ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በቁጥር አ/አከፀ 18 /03/ 128 ለባልደረሳስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በፃፈው ደብዳቤ ሰልፉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቀባይነት እንዳለገኘ ምላሽ የሰጠ ሲሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም በግልባጭ አሳውቋል ብሏል፡፡
ስለሆነም ተቀባይነት ያላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውሶ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉም ሆነ መረጃውን እያሰራጩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡
በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!