የኢትዮጵያ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዓውደ-ጥናት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ጉዳይን በሚመለከት ከጥር 19 እስከ 21 ቀን 2013 በአዲስ አበባ ዓውደ-ጥናት ተካሂዷል።
በዓውደ-ጥናቱ በዋናነት ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ሲካሄድ የቆየውን የድንበር ዳግም ማካለል ጉዳይ በነባር የሁለትዮሽ መድረኮች በሰላማዊና በዘላቂ መልኩ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።
በዓውደ-ጥናቱ ላይ የድንበር ጉዳዩን በተመለከተ የተቋቋሙት የዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች እና ብሔራዊ የጥናትና ምርምር ባለሙያዎች ቡድን አባላት ተሳትፈዋል፡፡
ባለፉት ሶስት ቀናት በተካሄደው አውደጥናት በድንበር ዳግም ማካለል ዙሪያ ሙያዊ ውይይት ተደርጎል።
በተጨማሪም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የህዝብ ለህዝብ ትስስር፣ የታሪክ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት መካሄዱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!