ኮርፖሬሽኑ በ2013 ግማሽ ዓመት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
በግማሽ ዓመቱ ለ19,757 ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩንም ገልጿል፡፡
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት 83,972,421 የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተቻለ ሲሆን 548,036 የአሜሪካ ዶላር የሚሆነው የግል የአደጋ መከላከያ መሣሪያ ምርት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከውጭ ሀገር ገበያ ተገዝተው ለሀገር ውስጥ ገበያ ሊቀርቡ ይችሉ የነበሩ ምርቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ማምረት እንዲችሉ በማድረግ 20,325,897 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሥራ የጀመሩ ሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች ማምረት ከጀመሩበት ግዜ አንስቶ እስከ አሁን 571,004,188 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ችለዋል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ኮርፖሬሽኑ ለ19,757 ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በኮርፖሬሽኑ በአጠቃላይ የፋብሪካ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ70 ሺህ በላይ ዜጎች ስራ ዕድል እንዲያገኙ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት አምስት ዓመታት 13 ያህል ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት 11 ያህሉን ወደ ምርት ሂደት ማስገባት ያስጀመረ ሲሆን የግል ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚዎችን በመደገፍ የሚጠበቅበትን እያከናወነ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡
በሚቀጥሉት ጊዚያትም በኮርፖሬሽኑ የተገነቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ሙሉ በሙሉ ውጤታማ በማድረግ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ በትኩረት ይሰራል ተብሏል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2013 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወር የስራ ዕቅድ አፈፃፀሙን በድሬዳዋ ከተማ ገምግሟል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!