የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 5ኛ አመት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 5ኛ አመት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ኢብራሂም፣ ምክትል አፈ ጉባኤ ፈርዶሳ መሀመድ እንዲሁም የምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት ነው እያካሄደ የሚገኘው።
በክልል ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን አምስት አጀንዳ በማፅደቅ ነው መደበኛ ስብሰባውን የጀመረው።
ምክር ቤቱ በጉባኤው የ11ኛውን መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣ የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት አመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ማዳመጥ፣ ለፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ የካፒታል በጀትን ማፅደቅ እንዲሁም የክልሉ ካቢኔ አባላትን ሹመትና የተለያዩ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!