Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የ”እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የ”እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች ጀመራል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን እና በፍጥነት የሚዛመት አዲስ የኮሮናቫይረስ መገኘቱን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው፥ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሰሞን የጥንቃቄ እርምጃዎች በተገቢው መልኩ ሲተገበሩ ቢቆዩም በቅርቡ ግን መዘናጋቶች መተስተዋላቸውን ገልጸዋል።

ይህ መዘናጋት ዋጋ እንዳያስከፍል “የእንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ንቅናቄ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በንቅናቄው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያሉ ተመሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ሠራተኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አቅራቢያ በእግር በመጓዝ “እንድናገለግል ማስክ ያድርጉ” የሚል ግንዛቤ ይሰጣሉ ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.