ጠ/ሚ ዐቢይ ለተደረገላቸው የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና አቀረቡ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “በመላው ኦሮሚያ ስለተደረገው የአብሮነት ድጋፍ ድምጽ ከልብ አመሰግናለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ገፃቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
“የመንግስት ልዩ ተልዕኮ ህዝብን ማገልገል ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየደረጃው ያለን የህዝብ አገልጋዮች ከእንደዚህ አይነት ድጋፍ የምንማረው እና መገንዘብ ያለብን ሀላፊነታችንን በአግባቡ እንድንወጣ የህዝብ ጥሪና አደራ እንዳለብን ሊሆን ይገባል” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለታየው እና ለነበረው ሰፊ ንቅናቄ መላው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪን በማህበራዊ ገፃቸው አመስግነዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!