Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ጀማል በከር በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሮ እስያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን የኢፌዴሪ የቆንስላ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር ጀማል በከር በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሮ እስያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር በኢትዮጵያና በባህሬን መካከል ያለው ሁለትዮሽ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖኖሚ፣ የማህበራዊና ባህላዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ግንኙነቶች በሚጠናከርበት ዙሪያ ከዳይሬክቴሯ ጋር በጥልቀት ተወያይቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አምባሳደር ጀማል ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ መልሶ ግንባታና ማቋቋም የሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በህዳሴ ግድብ ፍትሃዊና ምክንያተዊ ተጠቃሚነትና ትብብርን መሰረት ያደረገ ተጠቃሚነት እንዲኖር በአፍሪካ ህብረት እየተደካሄደ ባለው ድርድር እንዲፈታ ፍላጎቷ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮ-ሱዳን የተፈጠረውን የድንበር አለመግባበት ለመፍታት ከዚህ ቀደም የተወሰዱ ታሪካዊ እርምጃዎች በተለይም በጋራ የድንበር ኮሚሽን በኩል ችግሩን ለመፍታት ስለተሰራው ስራ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ነገር ግን በቅርቡ የሁለቱን ሃገራት ታሪካዊ ግንኙነትና አብሮነት በሚጻረር አኳኋን ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት መያዟን በመጥቀስ ሱዳን የያዘችውን መሬት እንድትለቅና አለመግባባቱ በሰላማዊ መንገድ በተቋቋመው የጋራ የድንበር ኮሚሽን በኩል እንዲፈታ የኢትዮጵያ አቋም መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሮ እስያ ዳይሬክትር ሙና አባስ መሐሙሁድ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽና ቀጠናዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ፤ አካባቢያዊና አለም አቃፍ ግንኝነቶች ይበልጥ ለማጠናከር በቅርበት ከአገራችን ጋር ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ተገቢና መንግስታቸው የሚደግፍ መሆኑን ገልጸው፥ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ ያሉ ልዮነቶችን እና የኢትዮ ሱዳን ድንበር አለመግባባቶችን በድርድርና በሰላማዊ መንገድ እንደሚፈቱ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሃገራቱ መካከል ያለው ትስስር እንዲጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት በመፈራረም ህጋዊ የሰው ዝውውር እንዲኖር፥ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይ ወደ ባህሬን እንዲሁም የባህረ ሰላጤው አየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በረራ በሚጀምሩበት ሁኔታ ዙሪያ መግባባት መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.