Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት በሆነው ኮቪድ19 ዙሪያ መወያየታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ እና ጀርመን መካከል ያለውን የልማትና የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.