Fana: At a Speed of Life!

የአስም በሽታ ክብካቤን ሊያሻሽል የሚችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምምነቱ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአስታራ ዘኔካ እና ከኢትዮጵያ ቶራኪክ ማህበር ጋር የተፈረመ የሶስትዮሽ ስምምነት ነው፡፡

በስምምነቱ መሰረት የተለያዩ የአስም ህክምና መመርመሪያ ማሽኖች ከተሟላ ስልጠና ጋር ይካተታሉ፡፡

በተጨማሪም 47 የመመርመሪያ ጣቢያዎች በአስትራ ዘኔካ ይገነባሉ ህብረተሰቡም በሙያ ትግበራ እና አቅም ልማት ውስጥ ይሳተፋል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ስምምነቱ የአስም እንክብካቤን አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚወስድ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡

አያይዘውም ከአስተራ ዘኔካ እና በዚህ ዘርፍ ውስጥ ካሉ ሁሉም ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠር እና ሁሉን አቀፍ ፖሊሲ ማዘጋጀት ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.