በቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ732 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ732 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ።
ባለፉት ወራት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲዘዋወር የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ በመጨረሻም በቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ያለውን ቆይታ አጠናቋል።
በዋንጫ ርክክብ ስነስርዓቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተገኝተዋል።
ባለፉት 6 ወራት በከተማዋ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ ከዚህ ቀደም ያልታየ እና የሕዝቡ ተሳትፎ በስፋት የታየበት መሆኑን አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተናግረዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በነበረው ቆይታ በአጠቃላይ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!