ኢትዮጵያና እስራኤል በመረጃና ደህንነት ዘርፍ የጀመሩትን ሁሉን አቀፍ ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመሰገን ጥሩነህ ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የእስራኤል የመረጃና ደህንነት ተቋም ሞሳድ የጀመሩት ሁሉን አቀፍ የትብብርና የአጋርነት ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ ስለሚቀጥልባቸው ጉዳዮች መወያየታቸውን አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተቋማቸው ከእስራኤሉ አቻ የመረጀና ደህንነት ተቋም ጋር በመረጃ ልውውጥ፤ ሽብርተኝነትን በጋር በመከላከል እንዲሁም በአቅም ግንባታና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የጀመረው የትብብር ማዕቀፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ወቅት ለተሰናባቹ አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ገልጸዉላቸዋል፡፡
የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ እስራኤል በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ላይ ወሳኝ ሚና ካላት ኢትዮጵያ ጋር በመረጃና ደህንነት ዘርፍ ተባብራ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎቷን በቆይታችው ወቅት ማሳካታችውን አንስተዋል፡፡
በቀጣይ በኢትዮጵያ እስራኤል ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን ለሚሾሙትም ይህን ተመሳሳይ የትብብር ተልዕኮ እንዲያስቀጥሉ መልዕክታቸውን እንደሚያስተላልፉም ነው ያስረዱት።
የእስራኤል የደህንነት ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይቫርካን እንዲሁም በኢትዮጵያና በአፍሪካ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ ኢትዮጵያና እስራኤል በመረጃና ደህንነት ዘርፉ ያላችውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት በ2013 ዓ.ም መፈጸማቸውም አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በላከው መረጃ አስታውሷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!