ብልፅግና ፓርቲ እና የሩሲያው ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልፅግና ፓርቲ ከሩሲያው ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ጥብቅ ወዳጅነት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ እና በፓርቲ ደረጃ ሊከወኑ የሚገባቸውን ጉዳዮች በጋራ ለመከወን የሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ያተኮረ መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል።
ይህም ሁለቱ ፓርቲዎች መርህ ላይ መሰረት ያደረገ ግንኙነትን እንዲያዳብሩ፣ ከየትኛውም ጣልቃ ገብነት የፀዳ ግንኙነትን እንዲፈጥሩ ብሎም ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።
ስምምነቱን በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ዋና ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ እና የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ አንድሬ ክሊሞቭ ተፈራርመውታል፡፡
በሀገር ደረጃ ብልፅግና ፓርቲ እየሰራቸው ያሉ የለውጥ ስራዎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ በዚህ ወቅት ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል።
በተለይም ነባራዊ ሁኔታዎችን ገምግሞ ብልፅግና ፓርቲ እየተከተለ የሚገኘው አማካይ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ዴሞክራሲ ቁልፍ ሚናን እንደሚጫወት እና ለዚህም መሳካት ከሩሲያው ዩናይትድ ፓርቲ ጋር በጋራ የመስራት ፍላጎት ብልፅግና ፓርቲ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ አንድሬ ክሊሞቭ በበኩላቸው፥ ፓርቲያቸው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመስራት ዝግጁነት እንዳለው ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!