የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ መንግስት እየሰራ ላለው ስራ ድጋፍ ሲያደርግ ለነበረው ህዝብ ምስጋና አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከለውጡ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ፓርቲውና መንግስት ከህዝቡ ጋር ሆኖ እየሰራ ላለው ስራ በተለያየ መልኩ ድጋፍ ሲያደርግ ለነበረው ህዝብ ምስጋና አቅርቧል።
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ከለውጡ በኋላ እየተሰራ ላለው ስራ እውቅና ለመስጠት ላደረገው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አመስግነዋል፡፡
የተጀመረው ለውጥ ቀጣይ እንዲሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
የድጋፍ ሰልፉን ተከትሎ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሰልፉ ላይ አላግባብ ስማችን ተነስቷል ብለው ላቀረቡት ቅሬታ ፖርቲያችሁ ምን ምላሽ አለው ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄም÷ የድጋፍ ሰልፉ መንግስት የጠራው ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ፍላጎት የወጣና ከ25 እስከ 30 ሚሊየን ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ነበር ያሉት ኃላፊው በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተነሳው ሀሳብም የህዝብ ነዉ ብለዋል።
ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ተከትሎ ከፖርቲዎቹ ቅሬታ ቀርቧል ብሎ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎም አሰራሩን በጠበቀ መልኩ ፖርቲው ከቦርዱ ጋር የሚነጋገር መሆኑን ገልፀዋል።
በትዝታ ደሳለኝ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				