Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመችው ወረራ ታሪካዊ ስህተት ነው – አምባሳደር ይበልጣል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመችው ወረራ ከሞራል፣ ከህግ ብሎም ሁለቱ ሀገራት ካላቸው የቆየ ወዳጅነት አንጻር ሲታይ ታሪካዊ ስህተት መሆኑን በሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ።

ወቅታዊ የኢትዮ-ሱዳን ጉዳይን በሚመለከት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በተለይ ለኢቲቪ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ሱዳን በፈረንጆቹ 1972 በሁለቱ መንግስታት የተደረሰውን የድንበር መርህ በጣሰ መልኩ ወረራ ፈጽማ ጉዳት አድርሳለች ብለዋል።

በወረራው በንብረት እና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል ያሉት አምባሳደሩ ሱዳን በፈጸመችው ወረራ በግምት እስከ 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ጉዳት ማጋጠሙን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ አሁንም ችግሩን በሰላም እና በመነጋገር ለመፍታት ዝግጁ ናት ያሉት አምባሳደሩ፥ ይህ የማይሆን ከሆነ ራስን የመከላከል ህጋዊ መብቷን እንደምትጠቀምም አስረድተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.