ፍርድ ቤቱ በእነጃዋር መሃመድ የችሎት ሂደት ላይ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ ችሎት መታደምን ከለከለ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ በእነጃዋር መሃመድ የችሎት ሂደት ላይ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ ችሎት መታደምን ከለከለ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት በነበረ ቀጠሮ ላይ ቤተሰቦቻችን በለበሱት ልብስ በችሎት ካልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላችን አንሰጥም ሲሉ ተከራክረው ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱም ይህን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ የያዘ ሲሆን፥ በዛሬው እለትም ማንኛውም በችሎት የሚታደም አካል አድማ የሚመስሉ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ ችሎት መታደም እንደማይችል ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም ችሎቱ ገለልተኛ እና ነፃ ሆኖ የሚዳኝበት እንደመሆኑ እንደዚህ አይነት አልባሳትን ለብሶ መግባት አይቻልም ሲልም ክልከላ ጥሏል፡፡
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የወንጀል ችሎትም፥ የተጠርጣሪዎቹን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለየካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				