Fana: At a Speed of Life!

ለአቶ ጃዋር መሃመድ አራት የሞባይል ሲም ካርዶችን ሊያቀብሉ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብለው ፍርድ ቤት የቀረቡት ሃምዛ ጀማል ጉዳያቸው ታይቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በሚገኙት ለአቶ ጃዋር መሃመድ አራት የሞባይል ሲም ካርዶችን ሊያቀብሉ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብለው ፍርድ ቤት የቀረቡት ሃምዛ ጀማል ጉዳያቸው ታይቷል፡፡
ተጠርጣሪው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ የቀረቡ ሲሆን ከሁለት ጊዜ በላይ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል፡፡
ተጠርጣሪው አንድ በኦ .ኤም.ኤን ድርጅት ስም የወጣ እና ሶስት በግለሰብ ስም የወጣ የሞባይል ሲም ካርድ ማረሚያ ቤት በመሄድ ለአቶ ጃዋር ሊያቀብሉ ነበር ተብለው በተደረገባቸው ምርመራ፥ ከአቶ ጃዋር እና ከኦ .ኤም.ኤን ሚዲያ ጋር በተያይዘ የተለዋወጧቸው የስልክ መልዕክቶች ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቋም ማምጣቱንም መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል፡፡
የምርመራ መዝገቡንም ለዐቃቤ ህግ ልኮ እየተመለከተ መሆኑን የገለፀው መርማሪ የሰው ማስረጃ ከማረሚያ ቤት አስተዳደር አመራሮች እና በእለቱ ጥበቃ ላይ ከነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ቃል የመቀበል ስራ መስራቱን ገልፆ ከእርሳቸው ጋር በትብብር ሲሰሩ ነበር የተባሉ ግብረ አበሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ቀሪ የምስክር ቃል ለመቀበል ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪው ከጠበቃቸው ጋር የቀረቡ ሲሆን እስካሁን ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ጊዜ በቂ መሆኑን ጠቁመው የሚያዙት ግብረ አበሮች ማንነታቸው ሳይገለፅ ለመያዝ ተብሎ ተጠርጣሪውን አስሮ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡
ተጠርጣሪው ጭሮ ከተማ የሚኖሩ እና በጫት ንግድ መሰማራታቸውን ጠቅሰው አሁን በሚኖሩበት አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቋሚ አድራሻ ስላለኝ ዋስትና ይሠጠኝ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም የምርመራ መዝገቡን አስቀርቦ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለየካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.