Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ነዋሪዎች በትግራይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ  

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ነዋሪዎች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚውል ከ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አበረከቱ፡፡

የክልሉ ተወካዮች ከነዋሪዎች የተሰበሰበውን ድጋፍ ዛሬ በመቀሌ ተገኝተው ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስረክበዋል፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰማን ሽፋ ከነዋሪዎች የተላከውን 3 ሺህ 200 ኩንታል የስንዴ ዱቄትና የቅንጬ እህል ማድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡

“መደጋገፍ የኢትዮጵያዊነት እሴት ነው” ያሉት አቶ ሰማን÷ ከትግራይ ሕዝብ ጎን በመቆማቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ የደቡብ ክልል ነዋሪዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ የሕዝቦች መተሳሰብ ከወሰን በላይ መሆኑን ያየንበነት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

“አብሮነት የሠላም ተምሳሌት ነው” ያሉት ዶክተር ሙሉ ÷ ድጋፉ የህዝቦች አንድነት ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።

የትግራይ ሕዝብ ድጋፍ በሚሻበት ጊዜ የደቡብ ክልል ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ሌሎች ክልሎችም ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የኦሮሚያ ክልል ለትግራይ ክልል ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.