Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የሚደረገውን ውይይት አጠናክራ ትቀጥላለች – ኢንጂነር ስለሽ በቀለ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚነሱ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት የምታደርገውን ጥረት እንደምትቀጥል የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ገለጹ።

ዶክተር ስለሺ ከአልጀዚራ ዓረብኛ ቋንቋ ስርጭት ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም ኢትዮጵያ ግድቡን በተመለከተ የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በውይይት መፈታት እንዳለባቸው ፅኑ አቋም ይዛለች ብለዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ግድቡን በተመለከተ መተማመን ያለበት ድርድር እንዲቀጥል ፍላጎቷ መሆኑን ጠቁመው፥ ከዚህ በተቃራኒው ግን በግድቡ ጉዳይ ላይ ውስብስብና አላስፈለጊ ጉዳዮች ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል።

ከታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ጋር በተካሄደ ውይይት የቴክኒክ ጉዳዮችን በተመለከተ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

በግድቡ ላይ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት እየተካሄደ ያለውን የሶስትዮሽ ድርድር በተመለከተም ኢትዮጵያ በህብረቱ የሚካሄደው ድርድር እንዲቀጥል እየሰራች መሆኗን አስረድተዋል።

በዚህ ሂደት ግን ሱዳን ባለፉት ሰባት ወራት ውይይቱ ሰባት ጊዜ እንዲቋረጥ ማድረጓን አንስተዋል፤ ኢትዮጵያ በህብረቱ የሚካሄደውን ድርድር አስተጓጉላለች ተብሎ የሚወራው ወሬ ሃሰት መሆኑን በመጥቀስ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያን ቀጣይ የመልማት መብት የሚጻረር ማንኛውንም አይነት አንቀጽ በሕግና ደንብ ውስጥ ማካተት ተቀባይነት እንደማይኖረውም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ግድቡ በቀጠናው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚካሄድ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል።

የግድቡ ግንባታ መጠናቅቅም የሃይል አቅርቦት እጥረት ያለባቸውን ኢትዮጵያውያን ችግር እንደሚያቃልልም አውስተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.