Fana: At a Speed of Life!

ራይዚንግ ኢትዮጵያ ንቅናቄን አስመልክቶ የምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃገሪቱን ገጽታ በተሻለ መልኩ ማስተዋወቅን ዓላማ አድርጎ የተጀመረው “ራይዚንግ ኢትዮጵያ” ንቅናቄ በቱሪዝም ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ፣ በባህል፣ በኢንቨስትመንት፣ በበጎ አድራጎት እና በዳያስፖራ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ያከናወናቸውን ተግባራት እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ተቀራርቦ መሥራት ንቅናቄውን ውጤታማ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

የምክክር መድረኩ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ገጽታ በበጎ መልኩ በማስተዋወቅ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በባህል ትውውቅ፣ በዳያስፖራ ቢዝነስ የኢንቨስትመንትና የፋይናንስ ፍሰትን ማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የቱሪስት ጉብኝት ቅንጅትና ፓኬጅን አተገባበር ያሉት ችግሮች መፈተሽ እንዲሁም በራይዚንግ ኢትዮጵያ ዙሪያ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን መገምገም፣ በኮቪድ 19 ምክንያት የተጎዳውን የቱሪዝም ማህበረሰብ ሞራል ማነቃቃትና የቱሪዝም ዘርፍ ስፖንሰር የሚያደርጉ ተቋማትን መለየትም የመድረኩ አላማ ነው።

ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት፣ ምድረ ቀደምት አምባሳደሮችን ለመሰየም መስፈርቶችን በመለየት እንደ ማሌዥያ፣ ፊሊፕንስ እና ኬንያ ያሉ ሃገራት የመለያ አምባሳደር አሰያየም ተሞክሮ መውስድ እና ለምድረ ቀደምት አምባሳደርነት የሚሰየሙ ግለሰቦች የስራ ድርሻ፣ ተጠሪነትና ተጠያቅነት ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስ ዲፕሎማሲና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ ለምድረ ቀደምት አምባሳደሮች ለአሰያየም የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ብቃትና ስብዕናን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚዘጋጅ ገልፀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.