በድሬዳዋ ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ በአራት ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮች ላይ ጉዳት ደርሷል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ትናንት ምሽት 2 ሰአት ገደማ አሸዋ ሲጋራ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ በአራት ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
የድሬዳዋ ፖሊስ እሳት አደጋ ተከላካይ ዲቪዥን በፍጥነት ቦታው ላይ በመድረሱ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የእሳት ቃጠሎውን መቆጣጠር ተችሏል፡፡
ፖሊስ የቃጠሎውን ምክንያትና የንብረት ጉዳት መጠን ለይቶና አጣርቶ እንደሚገልጽም አስታውቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				