Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስትሯ ከተመድ ዋና ጸሀፊ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ልዩ መልዕክተኛ ፓርፌይት ኦናንጋ-አንያንጋ ጋር ተወያዩ፡፡
ወይዘሮ ሙፈሪሃት በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት አብሮነትንና ሀገራዊ መግባባትንና ለማዳበር ብሎም ለዘመናት የኖሩ ድንቅ አዋሀጅ እሴቶችን ለማበልጸግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ልዩ መልዕክተኛው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄዱ ያሉ የማህበረሰብ ተኮር እና የልሂቃን የምክክር መድረኮች እንዲሁም ወጣቱ ከራሱና ከቤተሰቡ አልፎ በማህበረሰብና ሀገር መስተጋብር ማዕቀፍ ውስጥ በመልካምነት፣ በበጎነት፣ አብሮነት እና በፍቅር ማነጽን እሳቤ አድርጎ የተቀረጸውን የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም አካሄድ ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ልዩ መልዕክተኛው የኢትዮጵያ መንግስት ለዘላቂ ሰላም አስተማማኝ የሆነ አዎንታዊ ለውጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።
በተጨማሪም የህግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ዙሪያም ውይይት ያደረጉ ሲሆን በሚያስፈልጉ ሁለንተናዊ ድጋፍ ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሰላም ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ ወዳጆች አብሮነት ሃገሪቱ ትክክለኛው የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን ከማረጋገጡም በላይ በሀገሪቱ እንዲመጣ ለታለመው አወንታዊ ሰላምና ለውጥ ተጨማሪ ድጋፍ፣ ተስፋና ብርታት ይሆናል ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ላለው ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ፣ መንግስትና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.