የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው
የአዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
በግምገማው በተያዘው አመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የታቀዱ ግቦች በምን ያክል ደረጃ ተፈፃሚ ሆነዋል የሚሉ ነጥቦች ይነሳሉ ተብሏል።
በዚህም በስድስት ወሩ የከተማዋን ቁልፍ የማህበራዊ ችግሮችን የመፍታት፣ ህገ ወጥነትን የመከላከል እና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ አፈፃፀሞች እንደሚነሱም ይጠበቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የከተማዋን ቁልፍ ማኅበራዊ ችግሮች ለመፍታት፣ ሕገ ወጥነትን ለመከላከል እና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በኩል ለተመዘገቡት አፈጻጸሞች አጽንኦት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ግምገማው የዓመቱ እቅድ ሲታቀድ የኅብረተሰቡን ጥያቄ ማእከል በማድረግ ከተቀመጠው ግብ አንጻር የተፈጸመ መሆኑን መገምገም፣ በተለይ ባለፉት ስድስት ወራት በመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ፣ አሠራር ጠብቆ መሥራት፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ አመራሩ ተቀናጅቶ እና ተናብቦ ከመሥራት አንጻር የነበሩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች ምን እንደሚመስሉ መፈተሽ አለበት ሲሉም ነው የተናገሩት።
ይህ ግምገማ ከሌላው ጊዜ የሚለየው ከየደረጃው ወደ ላይ የመጣውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ከተለያየ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የተደረገበት እንዲሁም በድጋፍ እና ክትትል የታገዘ በመሆኑ፣ አንገብጋቢ እና የሕዝብን ጥያቄ መሠረት ያደረጉ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በይስማው አደራው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				