በመዲናዋ የፊታችን እሁድ ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን ይከበራል
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን እሁድ “መንገድ ለሰው” ከተሽከርካሪ ነጻ ቀን ይከበራል፡፡
ከተሽከርካሪ ነጻ መንገዶች ቀን ዋና አላማ ሞተር አልባ እንቅስቃሴ በማበረታታት አማራጭ የትራንስፖርት መንገድ ማበረታታት ነው ተብሏል፡፡
እኔዲሁም የትራፊክ አደጋ የማይከሰትባት ከተማን መፍጠር: ለኑሮ ምቹና ከብክለት የፀዳ ከባቢ አየር እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘዴን መፍጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት ፕሮግራም የሚካሄድባቸው ቦታዎች
1. ልደታ
2. ከሜክሲኮ አደባባይ በሸበሌ እስከ ብሄራዊ ትያትር
3. ከስድስት ኪሎ እስከ ሚኒሊክ ሆስፒታል
4. በስፔን ኤምባሲ መነን ትምህርት ቤት
5. ከለቡ ጀሞ
6. ከፊጋ ሳሚት መብራት ናቸው ተብሏል
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				