Fana: At a Speed of Life!

የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር እና ኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጁት ሃገር አቀፍ የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ ሉዓላዊነቷ የተከበረና ጥቅሟ የተረጋገጠ ሃገር በመገንባት ሂደት የምሁራን ሚና እና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም ለማስከበር በታሪክ በተደረጉ ተጋድሎዎች በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ የዜጎች ብሄራዊ ሃላፊነት በሚል ርዕስ ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

በተጨማሪም የህዳሴ ግድባችን አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችንን ከማስጠበቅ አንጻር የዜጎች የአርበኝነት ተሳትፎ አስፈላጊነት እና በሃገር በቀል እውቀቶችና ልምዶች ውስጣዊ ችግሮቻችን ከመፍታት አንጻር የባህል ተቋማት ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው አተኩሮ እየተካሄደ ያለው፡፡

በውይይቱ ላይ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ብሔራዊ ጥቅሟ እና ደህንነቷ ለተረጋገጠች ኢትዮጵያ ሁሉም የእምነት፣ የፖለቲካና ማንኛውም ልዩነት ሳያግደው ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ምሁራን ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ በከፍተኛ ኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በፀጋዬ ንጉስ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.