በጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት 12 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ድርሻ መሆኑ ተለየ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት 11 ነጥብ 99 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ድርሻ መሆኑን ለመለየት መቻሉን ገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ለ22 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌደሬሽን ምክር ቤት በመሻሻሉ ምክንያት ባለፉት 6 ወራት 11 ቢሊየን 991 ሚሊየን 401 ሺህ 706 ለክልሎች እንደሚደርሳቸው ተገልጿል፡፡
ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ስድስት ወራት አንፃር ሲታይ የብር 8 ቢሊየን 681 ሚሊየን 102 ሺህ ዕድገት አለው ተብሏል፡፡
ይህም በመቶኛ ሲሰላ 262 ነጥብ 25 በመቶ ዕድገት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የገቢው ምንጭ ከኤክሳይዝ፣ ከተርን ኦቨር፣ ከተጨማሪ እሴት እና ከንግድ ትርፍ ግብር ታክሶች ብቻ የተሰበሰበ ነው ተብሏል።
የጋራ ገቢው ድርሻ ያደገው የጋራ ገቢ ማከፋፈያ ቀመሩ በመቀየሩና የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ተናግረዋል።
የጋራ ገቢዎችን ለፌደራል እና ለክልሎች እንዲከፋፈል በፌዴሬሽን ምክር ቤት በተቀመጠልን የማከፉፈያ ቀመር መሰረት በስድስት ወራት የተሰራ እና አሁን ከተደረሰበት ውጤት ላይ መድረሱን ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!