በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፊቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ ነገ ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ምርቱን ለሸማቹ ያቀርባል።
የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይነህ ክንዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የዘይት ፋብሪካው 60 በመቶ የሃገሪቱን የዘይት ፍላጎት የመሸፈን አቅም ያለውና ለምግብ ዘይት ይወጣ የነበረውን 30 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ያስቀራል ብለዋል።
በአማራ ክልል ቡሬ ከተማ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ ግንባታው በ30 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ለ3000 ሰዎች የስራ እድልን ይፈጥራል።
ፋብሪካው የሃይል አቅርቦት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የግብዓት አቅርቦት ችግር እንደ ስጋት ተቀምጧል።
ነገ በሚመረቀው ፊቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ በቀን 200 ቶን የሰሊጥ ምርትን በተለያየ ደረጃ ማቀነባበር የሚችል፣ በቀን 96 ቶን ያህል ሳሙና የሚያመርት፣ የአትክልት ቅቤና ማርጋሪን እንዲሁም የጀሪካንና ፕላስቲክ ፋብሪካዎችን በውስጡ የያዘ ነው።
ነገ በሚካሄደው የምረቃ ስነስርዓት ላይ የፌደራልና የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
በዙፋን ካሳሁንና ቆንጂት ዘውዴ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!