በኦሮሚያ ክልል የኮቪድ ጥንቃቄ መስፈርቶችን ላሟሉ ሆቴሎች ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኦሮሚያ ክልል የኮቪድ ጥንቃቄ መስፈርቶችን ላሟሉ ሆቴሎች የእውቅና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠት መጀመሩን ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከአዳማና ከቢሾፍቱ ከተገመገሙ 38 ሆቴሎች ውስጥ ዝርዝር መስፈርቶችን አሟልተው የተገኙ ከአዳማ 4፤ ከቢሾፍቱ ደግሞ 3 ሆቴሎች የዕውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል።
የእውቅና አሰጣጡ አና አጠቃላይ የግምገማ ሂደቱ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ፣ በማሰልጠኛ ተቋሙ እና በክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በጋራ ተዋቅሮ የተሰራ መሆኑን እና ይህም ቀጣይ እንደሆነም መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በትናትናው ዕለት ኢትዮጵያ የጉዞ ደህንነት ማረጋገጫ ማህተም ከዓለም አቀፉ የጉዞ እና የቱሪዝም ካውንስል ማግኘቷ የሚታወስ ነው።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!