ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ፊቤላ የዘይት ፋብሪካን መረቁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት የማምረት አቅም ያለውን ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ መረቁ፡፡
የሀገሪቱን የምግብ ዘይት አቅርቦት 60 በመቶ የመሸፈን አቅም እንዳለው የተነገረለት ፊቤላ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከምግብ ዘይት ምርት በተጨማሪ የሰሊጥ ማቀነባበሪያ፣ ሳሙና እና የእንስሳት መኖ ያመርታልም ነው የተባለው።
በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የተገነባው ፋብሪካው 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ለ3 ሺህ ዜጎችም የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
እንደ አብመድ ዘገባ ፋብሪካው ምርቱን ከነገ ጀምሮ ለገበያ ያቀርባል ፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!