Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ የተጀመረውን ተግባር ለማስቀጠል ያለመ የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ የተጀመረውን ተግባርን ለማስቀጠል ያለመ በክልሉ የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈትቤት በሚኒስቴር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፣ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት በሚኒስቴር ማዕረግ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተገኝተዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይ በመተከል ዞን የህግ የበላይነት በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተጀመረውን ተግባር ለማሳለጥ የአመራሩን አቅም ለመገንባት ታሶቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑም ተገልጿል።
ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደር እና የወረዳ አመራሮች እንዲሳተፉ መደረጋቸውን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.