በቴክኖሎጂ የተደገፈ የዲፕሎማሲ ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሹመት ደብዳቤ ለተሰጣቸው አምባሳደሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ፣ በቪየና ኮንቬንሽን፣ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ በሃገሪቱ የዲፕሎማሲ ታሪክ ፣ በሃይድሮ ዲፕሎማሲ፣ በአፍሪካ እንዲሁም በቀጠናዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያተኮረ መሆኑም ታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አምባሳደሮቹ በቴክኖሎጂ የተደገፍ የዲፕሎማሲ ሥራ ማከናወን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ለዚህም የማህበራዊ ሚዲያን በስፋት መጠቀም እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ህግን ለማስከበር ከተወሰደው እርምጃ ጋር ተያያዞ የህወሓት ጁንታ ቡድን ከደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያሰራጩ ያሉትን የተሳሳተ መረጃ ለመመከት ከዳያስፖራ አባላት ጋር በመቀናጀት ትክክለኛ መረጃ ለተወከሉባቸው ሃገራት እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማዳረስ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባም ሚኒስትር ዲኤታዋ ገልፀዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!