ዘፈንና ሥነ ቃል ከሀገራዊ ፋይዳ አንፃር በሚል መሪ ቃል ሃገር አቀፍ አውደ ጥናት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመሆን ያዘጋጁት “ዘፈንና ስነ ቃል ከሀገራዊ ፋይዳ አንፃር” በሚል መሪ ቃል ሃገር አቀፍ አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ዘፈኖች የተለመደውን የዕለት ተዕለት ህይወት ከመግለጽ ባሻገር ታላላቅ ሃገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ለሀገር አንድነትና ለህዝቦች መቀራረብ የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ባህል እንዲጠና ፣ እንዲተዋወቅና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲውል በትጋት እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
በጉባኤው ዘፈንና ስነ ቃል ላይ ትኩረት ያደረጉ ጽሁፎች፣ በሙዚቃ ዙሪያ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ፍልስፍና እና የህይወት ተሞክሮ፣ ባህል እና ትውፊትን ከማሳደግ እና ከማስተዋወቅ አንፃር የተሰሩ ስራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎቸ ባሉ የስነ ቃል እና ዘፈን አጠቃቀም ዙሪያ የሙዚቃ ባለሙያዎች የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፣ ባህላዊ ሙዚቃዎች ላይ ባህልን ከማንፀባረቅ አኳያ የሚስተዋሉ ጉድለቶች ላይም ውይይት ተካሄዷል፡፡
በመድረኩ በባህላዊ ዘፈኖች ላይ ባህልን እና ትውፊትን ከማንፀባረቅ አኳያ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ የክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባና ዘመናዊ እና ባህላዊ የሙዚቃ ቅንብሮች ላይ ተቆጣጣሪ አካል ሊኖር እንደሚገባ መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
			 
				