Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዳያስፖራውን በማሳተፍ ማህበራዊ ችግሮችን መቅረፍ የሚቻልበት ዕድል ለማመቻቸት ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ባስተላለፉት መዕልክት ዳያስፖራው በሃገር ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ እንዲሳተፍ ማስተባበርና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ለኤጀንሲው ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዘርፍ ለመስራት ራሳቸውን ካደራጁ ማናቸውም ሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር ለመስራት ኤጀንሲው ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።

አያይዘውም ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከዳያስፖራው ጋር በመስራት ባዳበረው ረዥም ልምድና በዳያስፖራው ዘንድ ባለው ተቀባይነት እንዲሁም ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ሊያከናውን ያቀዳቸው ተግባራት ያላቸው ሃገራዊ ፋይዳ ታይቶ የመግባቢያ ሰነዱ መፈረሙን ጠቅሰዋል።
የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በበኩላቸው ከኤጀንሲው ጋር መግባቢያ ሰነዱን መፈራረማቸው ዳያስፖራውን ከድጋፍ ባሻገር ባሉ የልማት ስራዎች ላይ ለማሳተፍ ዕድል እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡

ብሁ ሃገራት በዳያስፖራቸው ተሳትፎ መለወጣቸውን ያነሱት ሲስተር ዘቢደር ከኤጀንሲው ጋር መስራታቸው ዳያስፖራውን በተደራጀ መልኩ በማስተባበር ለላቀ ሃገራዊ ግብ እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል ማለታቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.