Fana: At a Speed of Life!

6ኛው የሚጥል በሽታ ሳምንት “በሚጥል ህመም ለተጎዱ ድምጽ ነኝ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ብሄራዊ የሚጥል በሽታ ሳምንት “በሚጥል ህመም ለተጎዱ ድምጽ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ለስድስተኛ ጊዜ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና ፕሮግራሞች ይከበራል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የሚጥል በሽታ ህክምና የታማሚውን ቤተሰብና የህብረተሰቡን ድጋፍ እንደሚጠይቅ አስታውቀዋል፡፡

ይህም ድጋፍ በተገቢው ሁኔታ ሊተገበር የሚችለው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስለህመሙ ያለው የተሳሳተ አመለካከትና ግንዛቤ ሲለወጥ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ህሙማን በወቅቱ ወደ ጤና ተቋማት ሄደው ምርመራና ህክምና ሲያገኙና በህመሙ ምክንያት የሚከሰተው የአካል ጉዳትና ህመም መቀነስ ሲቻል ነውም ብለዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.