ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ጋር በትብብር እንደምትሰራ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ፌሌክስ ሺሴኬዲ ጋር በትብብር እንደምትሰራ አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ የእንኳን ደስ አለወት መልክዕት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ ለተመራጩ ሊቀ መንበር ድጋፍ ታደርጋለችም ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሊቀ መንበሩ ጋር በትብብር እንደምትሰራም አስታውቀዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ መልካም የስራ ዘመን ይሆንላቸው ዘንድም ተመኝተዋል፡፡
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን በመተካት ባለፈው ቅዳሜ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!