Fana: At a Speed of Life!

60 ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች አመራርነት እና አገልጋይነትን በተግባር ሊሰለጥኑ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁሉም ክልሎች በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ 60 ተማሪዎች አመራርነትን እና አገልጋይነትን በተለያዩ ተቋማት ተሰማርተው በተግባር እንደሚሰለጥኑ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ገለጹ፡፡

ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወጣቶቹን ከሚያሰለጥነው ሴንተር ፎር አፍሪካን ሊደርሺፕ ከተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር ተፈራርሟል ብለዋል፡፡

ወጣቶቹ 6 ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላቸዋልም ተብሏል፡፡

ፕሮግራሙ ለተከታታይ አምስት አመታት የሚቆይ ሲሆን በየአመቱ የወጣቶቹ ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.